በሀኪም የታዘዙ መድኃኒቶች በቀላሉ ያግኙ

እናንተ ጤናችሁን መጠበቅ ላይ ብቻ እንድታተኩሩ፣ እኛ ተግተን እንሠራለን።

 24 ሰዓት ክፍት ነን

ስለእኛ ማወቅ ይፈልጋሉ?

MedhanET የተባልው በአይነቱ ትልቅ እና በራዕዩ ለየት ያለ የመድሃኒት ማፈላለጊ እና የማዘዣ ፕላፎርም የበለፀገው በ2020 ዓ.ም. ነው። የተቋቋመበትም ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ሲታመሙ በሀኪም የታዘዘላቸውን መድኃኒቶች የማግኘት ችግርን ለመፍታት ነው። እነዚህ መድኃኒቶች የህመምተኞችን ህይወት የመታደግ አቅም ያላቸው ናቸው። የህሙማን ስጋት የሚፈጠረው መድኃኒቶችን አግኝተው እንዲገዙ የሚያስችላቸው ማዕከላዊ እና አስተማማኝ ስርዓት ባለመኖሩ ነው። የታዘዘላቸውን መድኃኒቶች የሚገመግምላቸውና የሚከታተልላቸው ወጥ የሆነ አካሄድ ባለመኖሩም ተጨማሪ የህሙማን ስጋት ምንጭ ነው። እኛ የፈጠርነውና የዘረጋነው ሥርዓት የመድኃኒት ግዢና አጠቃቀም ሂደቶችን በሙሉ በማቀናጀት ህሙማን በመሉ እንዲድኑ ለማገዝ ያለመ ነው።

አገር-በቀል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለደንበኞቻችን መድኃኒቶችን ከማግኘት ባሻገር የተለያዩ ሌሎች ጠቃሚ አገልግሎቶችንም እንሰጣለን። የደንበኞቻችን ጤንነት ስለሚያሳስበን የሚያስፈልጋችሁን እና የሚገባችሁን ህክምና እና ክትትል እያገኛችሁ መሆኑን ለማረጋገጥ አልመን በአቅማችን በሙሉ የምንችለውን ሁሉ በትጋት እንሠራለን።

ሠራተኞቻችን፣ ፋርማሲስቶቻችን እና ሀኪሞቻችን በሙያቸው የተካኑና እውቅና ያላቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ ስለ እያንዳንዱ ደንበኛችን ጤንነት የሚያስቡ በመሆናቸው ህሙማን እንዲድኑ የማገዝ ራዕያችንን እያሳካን እንገኛለን። 

ሥራችን

የታዘዘሎትን መድኃኒቶች በሲስተማችን ስር በሚገኙ ከ2000 በላይ የመድሃኒት አይነቶችና ባሉባችው ከ50 በላይ በሚሆኑ ፋርማሲዎች ፈልጎ ምላሽ የሚሰጥ ፕላትፎርም ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሃኪሞ በኛ ሲስተም ተጠቅሞ ማዘዣ ከላከ ከአስተማማኝ የፋርማሲ ኔትወርካችን አፈላልገን ያለበትን ቦታ በአጭር የጸሁፍ መልክት እናሳውቆታለን። በተቀናጀው አሠራራችን ህሙማን መድኃኒቶች ለማግኘት ሳይጨነቁ ጤናቸውን መጠበቅና መንከባከብ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ በማገዝ የመድኃኒቶች ማኔጅመንትና አጠቃቀም እንዲሻሻል በማድረግ ዓላማችንን እናሳካለን።