የትዕዛዝ መድኃኒቶች ማስታወሻ አገልግሎት

ህይወታችን በስራ፣ በትምህርት፣ በማኅበራዊ ኑሮ እና ውጣ ውረዶች የተሞላ ነው። በተከታታይ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ተጠቃሚዎች ከሆንን በኑሮ ተጠምደን መድኃኒታችንን መቼ መግዛትና መውሰድ እንዳለብን ልንረሳ እንችላለን። መድኃኒታችን አልቆብን ድጋሚ መግዛትም ሊያስፈልገን ይችላል። እንደ ደምበኞቻችን መድኃኒት አወሳሰድ እለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርኃዊ የመሳሰሉ ማስታወሻዎችን እንልካለን። ለመድኃኒት ደምበኞቻችን የሚወስዱት መድኃኒት ከማለቁ ከ3 እስከ 7 ቀኖች በፊት በአጭር የስልክ ጽሑፍ መልዕክት (ቴክስት) ማስታወሻ እንልካለን። እንደ ደምበኞቻችን ፍላጎት መድኃኒቶቹን ፈልገን እቤታቸው ድረስም እናደርሳለን።

በሚገባ። የማስታሻው ዓይነት በካላንደር አለርት፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት፣ በኢሜል እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ። ማስታወሻው የሚላክለት ሰው በታማሚው፣ በአስታማሚው፣ ወዘተ አድራሻ እንዲሆን በማድረግ፤ እና በየስንት ጊዜው ማስታወሻው እንዲላክ መምረጥና ማስተካከል ይቻላል።

ለመድኃኒት ደምበኞች የመድኃኒት ማስታወሻ አገልግሎት ነፃ ነው

ይህንን አገልግሎታችንን በቅርቡ ለማስጀመር እየተጋን ነው። አገልግሎቱን ለመጠቀም ፍላጎት ካሎት ከታች ያለውን በመጫን ይመዝገቡ።

ፍላጎት መመዝገቢያ

• በ patients@medhan.et ኢሜል ወይም በቴሌግራም ቻናላችን @medhanET ይጻፉልን።