የታዘዘሎትን መድኃኒቶች ያግኙ

ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቶችን በቀላሉ ማግኘት እንደማይቻል የታወቀ ነው። አብዛኞቻችንም የምንቸገርበት ጉዳይ ነው። ስንታመም ህመማችንን ማዳን ላይ ከማተኮር ፋንታ መድኃኒት ፍለጋ ስንንከራተት ውድ ጊዜያችንን ከማባከናችንም በላይ ጤናችን ላይ ተጨማሪ ጠንቆችን በመጨመር ህይወታችንን እስከማስክፈል ድረስ እያደረሰን ይገኛል። ህይወት አዳኝ መድኃኒቶችን በአቅራቢያቸው ባለማግኘታቸው ህይወታቸውን የሚያጡም ብዙ አሉ

ድርጅታችን MedhanET ይህን ችግር የተለያዪ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ላማቃለል ይጥራል።

ፋርማሲ ወይም መድኃኒት መሸጫ አይደለንም። እኛ የፈጠርነው ቴክኖሎጂ ታማሚዎች መድኃኒቶችን በቀላሉ ፈልገው የሚያገኙበት፣ የሚገዙበት እና የምናደርስበትን አገልግሎት ነው።

ለጊዜው ያለ ሀኪም ማዘዣ ወረቀት ትዕዛዞችን አንቀበልም። 

ለጊዜው አገልግሎታችንን በክፍያ ነፃ ነው።

ከበታች ያለውን ሊንክ በመጫን የፈለጉንት መድሃኒት በመፈለጊያ ቦታው ይጻፉ። ስፔሊንግ ቢሳሳቱም አያስቡ። ተቀራራቢ መልሶችን ይሰጦታል።

ከዚህ በተጨማሪም የፈለጉት መድሃኒት ያለበትን ፋርማሲ ካላገኙ ገየሀኪም ትዕዛዝ ወረቀቶትን ፎቶ አንስተው የሚጭኑበት ቦታ ከታች ያገኛሉ። አድራሻዎትን (ስልክ ቢያንስ) ለመሙላት ከታች ያለውን ይጫኑ።
 
የታዘዘሎትን መድሃኒት ይፈልጉ

የፈላጉትን መድሃኒ ፈቃድ ካላቸው መድኃኒት መሸጫዎች ያለበትን እና አድራሻ እንጠቁሞታለን። የሚፈልጉትን መድኃኒት ሲስተሙ ካላገኘው አፈላልገን ከ36-72 ሰዓታት ውስጥ ማግኘት አለማግኘታችንን እናሳውቆታለን።

መድኃኒቱን ካላገኘን ፡ የምናገኝበትን መንገድ ወይም አማራጮችን እንሳውቆታለን።

በ patients@medhan.et ኢሜል ወይም በቴሌግራም ቻናላችን @medhanET ይጻፉልን።