አጋሮቻችን

በአጋርነት በመሥራት እናምናለን። ከኛ ጋር በአጋርነት በመሥራት ቢዝነሶትን እና ደምበኞችን የሚጠቀሙ መሆኑን ካመኑበት ያነጋግሩን። በአጋርነት በመሥራት ሁሉም ተጠቃሚ በሚሆንበት ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በራችን ሁሌም ክፍት ነው።

የአቅርቦት አጋር

የአቅርቦት አጋር ምንድን ነው?
የአቅርቦት አጋር ሕጋዊ ቢዝነስ ሆኖ መድኃኒቶችንና የህክምና አቅርቦቶችን ለመሸጥና ለማከፋፈል ፍቃድ ያለው ተቋም ነው። ለምሳሌ ፋርማሲዎች፣ መድኃኒትና የህክምና አቅርቦት አከፋፋዮች፣ ክሊኒኮች እና ሆስፒታሎች። ከእናንተ ጋር በአጋርነት በመሥራት የተጠቃሚዎችን መድኃኒት ፍለጋ ለማቀላጠፍና ለማሻሻል እንፈልጋለን።

የአቅርቦት አጋር መሆን ጥቅሙ ምንድነው?
የአቅርቦት አጋራችን ሲሆኑ እኛ መድኃኒት ለመግዛት ሲንከራተቱ የነበሩ ደንበኞችን እናቀርብሎታለን። ተጨማሪ ቅርንጫፎች መክፈት ሳያስፈልጋችሁ በአገር አቀፍ ደረጃ መድኃኒቶችን እንድታከፋፍሉ እናስችላቹኋለን።

የአቅርቦት አጋራችን ሲሆኑ የሚከተሉትን ተጨማሪ ጠቀሜታዎች ያገኛሉ:-
• አስተማማኝ የገቢ ምንጭ፤
• የግብይት ወጪዎት ይቀንሳል፤
• የማርኬቲንግ ወጪዎትን ይቀንሳሉ።

አቅርቦት አጋራችን ለመሆን ከፈለጉ በ0993929107 ይደውሉልን ወይም በ partner@medhan.et ኢሜይል ይጻፉልን። 

የፈላጊዎች አጋር

የፈላጊዎች አጋር ምንድነው?
የፈላጊዎች አጋር ሕጋዊ ቢዝነስ ሆኖ አገልገሎት እና ምርቶችን የሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ያሉት ተቋም ነው። የMedhanET አጋር በመሆን ምርትና አገልግሎታችንን ለተጠቃሚዎች ማስተዋወቅ ትችላላችሁ። እንደ ድረ-ገጽ አበልፃጊዎች (ድቨለፐሮች)፣ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ባለቤቶች፣ የቴሌ ሜዲስን አገልግሎት ሰጪዎች እና ሌሎች ሚዲያዎች እና ጥቆማን በመሳሰሉት መንገዶች ማስተዋወቅ ይችላሉ።

በተለይ ለሶፍትዌር ድቨለፐሮች እና የቴሌ ሜዲስን አገልግሎት ሰጪዎች የMedhanETን ሲስተም API ስላበለፀግን ፡ APIዩን ተጥቅማቹህ የራሳቹን ፈጠራ ጨምራቹ መጠቀም ለምትፈልጉ በhttps://api.medhan.et/api-docs/ የሙከራ ዳታ እና ተጨማሪ መረጃ ታገኛላቹ። ለጊዜው ይህን API በነፃ መጠቀም ትችላላቹህ።

የፈላጊዎች አጋር መሆን ጥቅሙ ምንድን ነው?
የፈላጊዎች አጋራችን ሲሆኑ ተከታዮቻቹህን ወይም ታካሚዎቻቹህን የተሻለ አገልግሎት እና ተደራሽነቱ የሰፋ የመድሃኒት ማፈላለጊያ ፕላትፎም ጋር ስላገናኟቸው ጤናቸውን ከመታደግ በተጨማሪ ለአገልግሎታቹህ ደንበኝነት እንዲዳብር እና እንዲያድግ ያደርገዋል።

የፈላጊዎች አጋራችን ለመሆን ከፈለጉ በ0993929107 ይደውሉልን ወይም በ partner@medhan.et ኢሜይል ይጻፉልን።