የመድኃኒቶች አወሳሰድ ግምገማ

አብዛኞቻችን በተለያዩ ምክንያቶች ለአጭርና ለረጅም ጊዜ መድኃኒቶችን እንወስዳለን። ዳሠሣው በመድኃኒት ወሳጁ እና በዶክተር፣ በነርስ ወይም በፋርማሲስት በመሳሰሉ ባለሙያዎች መሀከል የሚደረግ ውይይት ነው። ዓላማው መድኃኒት ተጠቃሚው ከመድኃኒቶቹ የሚያገኘውን ጥቅም ይበልጥ ለማሻሻል ነው። መድኃኒት ተጠቃሚዎች መድኃኒቶቻቸውን:-
                 • እጅግ በበዛ መጠን እየወሰዱ ከሆነ፣
                 • ትክክል ባልሆነ አኳሃን እየወሰዱ ከሆነ፣ ወይም
                 • እጅግ ባነሰ መጠን እየወሰዱ ከሆነ፤
እነዚህን በማስተካከል ተጠቃሚነትን የሚያሻሽል ነው። ዳሠሣው መድኃኒት ተጠቃሚዎች የፈለጉትን ጥያቄያዎች ለመጠየቅ ጥሩ እድል ይሰጣቸዋል። 

መድኃት ከታዘዘሎት ጊዜ ጀምሮ የመድኒቶችዎን ዳሠሣ በባለሙያ ያላስደረጉ ከሆነ ቢያስገመግሙ ይመከራል። ከዚህ በተጨማሪ:-

• እድሜዎት ከ75 ዓመት በላይ ከሆነ፤
• እንደ ስኳር፣ አስም እና የሚጥል በሽታ ያሉ የረጅም ጊዜ ህመሞች ካለቦት፤
• በሆስፒታል የታዘዙ መድኃኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ፤
• በቅርቡ ከሆስፒታል የወጡ ከሆኑ፤ እና
• መድኃኒቶችዎ ላይ ትልቅ ለውጥ ተደርጎ ከሆነ፤

ግምገማውን እንዲያሠሩ ይመከራሉ። 

ለመድኃኒት ደምበኞች ይህ የመድኃኒቶች ግምገማ አገልግሎት በነፃ የሚሠጥ ነው።

ይህን አገልግሎታችንን በቅርቡ የምንጀምር ሲሆን፤ መድኃኒቶችዎን የማስዳሠሥ ፍላጎት ካሎት ከዚህ በታች ያለውን የግምገማ ፍላጎት መመዝገቢያ የሚለውን በመጫን ፍላጎቶን ያስመዝግቡ

ግምገማ ፍላጎት መመዝገቢያ

• የሚወስዷቸውን መድኃኒቶች እንዴትና መቼ እንደሚወስዷቸው ይዘርዝሩ።
• እዚህ ዝርዝር ውስጥ እንደ ህመም ማስታገሻ ያሉና ከሀኪም ትዕዛዝ ውጭ የሚገዙዋቸውና የሚወስዷቸውን መድኃኒቶች ያካትቱ።
• በግምገማው ወቅት እንዳይረሷቸው እንዲረዳዎት፣ የሚያሳስቦትን ጉዳዮችና መጠየቅ የሚፈልጉትን ጥያቄዎች ይጻፏቸው።
• የዳሠሣ ቀጠሮዎት መቼ፣ የት እና ከማን ጋር እንደሆነ ጠንቅቀው ይወቁ።

ከግምገማው የሚመነጩ አማራጮች በሙሉ በእርሶ ፍላጎትና ፈቃድ ብቻ የሚወሰዱ መሆኑን አይርሱ።

• በ patients@medhan.et ኢሜል ወይም በቴሌግራም ቻናላችን @medhanET ይጻፉልን።